ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተመስገን ገብሬ
[1902 - 1943]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ሕይወቴ(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ ከተማ በ1902 ዓ.ም. ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ። ጉብዝናቸው በዘመናዊ ትምህርት ሲከታተሉም ጎልቶ ወጥቷል፡፡ ከጎጃም አዲስ አበባም በመምጣት በሲውዲን ሚሽን ትምህርት ቤት ተማሩ በወቅቱ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡

ተመስገን በጋዜጠኝነት ሙያ ከመስራታቸውም በላይ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ቦታ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ወቅት በዐርበኝነት ከጠላት ጋር ተፋልመዋል፡፡ ሱዳን ተሰደው ገዳሪፍ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በልዩ ልዩ መልክ አስተምረዋል፡፡ ጣሊያን ከለቀቀች በኋላ የዘመናዊ አስተሳሰብና ዕድገት ዓላማዋ ዕውን እንዲሆን ፍፁም የለውጥ ዐርበኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡

ተመስገን “የጉለሌ ሰካራም” በሚል አጭር ልብወለዳቸው የመጀመሪያ የአገራችን አጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የጉለሌው ሰካራም ከመታተሙ በፊት “የካቲት 12” እና “አለቃ እውነቱ” የተሰኙ ሁለት አጫጭር ልብወለዶችን በጋዜጣ ላይ አውጥተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com