ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ስብሐትለአብ ገብረእግዚአብሔር
[1928 - 2004]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ዐምስት ስድስት ሰባት(ልብወለድ)
2.   ታከለ ታገለ(ታሪክ)
3.   ሰባተኛው መልአክ(ልብወለድ)
4.   እነሆ ጀግና(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ፋሺስት ኢጣሊያ ሀገራችንን በወረረበት 1927 ዓ.ም ገደማ ተፈጥረው የጥበቡን ከተማ በስራቸው ካስጌጡ ኢትዮዽያውያን መሃል አንዱ ደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር ነው። ሚያዚያ 27/1928 አድዋ አውራጃ ርባ ገረድ ከምትባል ስፍራ ከአቶ ገብረ እግዚአብሔርና ወ/ሮ መዓዛ ተወልደመድህን ከተወለዱት 11 ልጆች 7ኛ ሆኖ የተወለደው ስብሐት አድጎ የአንድ የአጭር ልቦለዶች ስብስብና የሦስት መካከለኛ ልቦለዶች "አምስት ስድስት ሰባት"፣"ሌቱም አይነጋልኝ"፣"ትኩሳት"፣ "ሰባተኛው መልአክ" ደራሲ ብቻ ሳይሆን ከ30 ለበለጡ ዓመታት ጋዜጠኛም ነበሩ።

ጋዜጠኛው ስብሐት በ"አዲስ ዘመን" ጋዜጣ፣ "ሄራልድ" ጋዜጣ፣ "መነን" መጽሔት ፣ "Addis Reporter" ጋዜጣ፣ "የካቲት" መጽሔት፣ "ቁምነገር" መጽሔት፣ "ለዛ" መጽሔት፣ "አዲስ አድማስ" ጋዜጣ፣ "ሮዝ" መጽሔት ላይ ከአምደኛነት እስከ ዋና አዘጋጅነት መስራት ብቻ ሳይሆን በሚከተለው የአጻጻፍ ስልት የራሱን አንባቢያን መፍጠር ችሏል።

ስብሐት በተለይም ተፈጥሯዊነት ከሚጎላበት የአፃፃፍ ስልቱና ሕይወቱንም እንደሚጽፈው ለማኖር በሚያደርገው አኗኗር ደጋፊና ነቃፊ የፈጠረ አወዛጋቢ ሰው ነው። ይሁንና ስብሐት ገ/እግዚአብሄር ማንም ይደግፈውና ይንቀፈው ለማንም ይጣምና ይምረር የራሱን የሕይወት መንገድ አስምሮ በዚያ ላይ ሲጓዝ የነበረ ደራሲና ጋዜጠኛ ነው።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1952 ዓ.ም የባችለር ዲግሪውን ካገኘ በኋላ ለሁለት አመታት የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሆኖ አገልግሏል። ምንም እንኳን ትምህርቱን ሳይጨርስ ቢመለስም ለከፍተኛ ትምህርት አሜሪካና ፈረንሳይ ሄዷል። ፈረንሳይ ትምህርቱን ባታስጨርሰውም "ትኩሳት"ንና "ሠባተኛው መልአክ"ን ሰጥታዋለች። ሆነም ቀረ ስብሐት በተለይም እሱ የህይወቱ ተልእኮ አድርጎ በያዘው ሥነ ጽሁፍ በየትም ደረጃ የተማረ ሰው ሊያበረክተው ከቢገባው በላይ ከፍ ያለውን ድርሻ ተወጥቷል ማለት ይቻላል። እንደ አፃፃፉ ሁሉ በአኗኗሩም ሕይወትን ከነብጉሯ መግለጽ ይወዳል። ስብሐትን ባህል፣ ይሉኝታና የሌሎች አስተሳሰብ ሳይሆን ህይወት ሊያውም የራሱን ህይወት ናት የምትመራው።ስለዚህም ይሆናል 70 ዓመት እድሜን ከዘለለ በኋላ ከአንዲት ወጣት ብን ያለ ፍቅር ውስጥ የገባው "እናም ተመቻችተናል" ያለው።

ምንጭ: "አዲስ ጉዳይ" መጽሔት ቅጽ 6 ቁጥር 129 ዿጉሜን 2004 ዓ.ም ልዩ እትም።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com