ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ፈላስፋው ቃየል ነው(ልብወለድ)
2.   እሬትና ማር(ልብወለድ)
3.   የድሆች ጠበቃ(ልብወለድ)
4.   ዳኞች በፍርድ ላይ(ልብወለድ)
5.   ባሌ መታኝ አለች ወይስ ፈታኝ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ በሸዋ ክፍለ ሀገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በ፲፱፳፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜም ትምህርታቸውን በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተል ከየንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።

ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ጥቅምት ፲፱፳፫ ዓ.ም. በወታደርነት ተቀጥረው ለአሥር ዓመታት፤ በሲቪል ፀሐፊነት ደግሞ ለሃያ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከ፲፱፶፫ ዓ.ም. ጀምሮ ድርሰት መጻፍ የጀመሩት ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል “ፈላስፋው ቃየል ነው”፣ “እሬትና ማር”፣ “የድሆች ጠበቃ”፣ “ዳኞች በፍርድ ላይ”፣ “ባሌ መታኝ አለች ወይስ ፈታኝ” የሚባሉት የገኙበታል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com