አጥናፍሰገድ ይልማ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር ልዩ ስሙ “ጥቾ” በተባለ ቦታ ግንቦት ፳፯ ቀን ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ቀ.ኃ.ሥ. ጢቾ ትምህርት ቤት በ፲፱፵፰ ዓ.ም. አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም በ፲፱፶፩ ዓ.ም. አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ት/ቤት ገብተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ፈጸሙ፡፡ በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ መንግሥት ተጨማሪ ዕውቀት ገብይተዋል፡፡ አጥናፍሰገድ ይልማ “የበደል ካሳ” በሚል ርዕስ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ አሳትመው ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |