ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ቀፀላ ወርቁ ፀሐይ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ለምን አትሞትም(ልብወለድ)
2.   የቂም እሽሩሩ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ቀፀላ ወርቁ ግንቦት ፲፫ ቀን ፲፱፴ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ቀ.ኃ.ሥ. ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርታቸውን በቀድሞ ቀ.ኃ.ሥ. ዩኒቨርሲቲ፣ በሂሳብ አያያዝና በሕይወት መድን ትምህርት ዘርፍ በማታው የትምህርት መርሐ ግብር ተከታትለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ ቀፀላ ወርቁ በኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበር በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትና በማኀበሩ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃትና በቀዳሚነት ተሳታፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ የማኀበሩ እንቅስቃሴ በተዳከመበት ወቅት እንኳን ከማኀበሩ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ያላቋረጡ፣ ጠንካራ ሥነ ምግባር የነበራቸው አባላችን ነበሩ፡፡ እኒህ አንጋፋ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ “የቂም እሽሩሩ”፣ “ለምን አትሞትም”፣ የተሰኙ ልቦለድ መጻሕፍት አሳትመው ለአንባብያን አበርክተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com