ፀሐይ መላኩ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፵፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን ጎንደር በቀዳማዊ ኃ.ሥላሴ ት/ቤት ተምረዋል።
“ቋሳ”፣ “አንጉዝ”፣ “ቢስራኄል”፣ የተሰኙ የረዥም ልቦለድ ሥራዎችን ለንባብ አብቅተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበር ባሳተመውና “የዘመን ቀለማት” በተሰኘው የሥነ ግጥም መድብልም፤ ሥራዎቻቸውን ከሌሎች ደራስያን ጋር አቅርበዋል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |