ከእንጦጦ እስከ ባሮ   ስለመጽሐፉ የተሰጠ አስተያየት  
Author:  ኣምባቸው ከበደ
Price:  50
BookStore:  Tesfaye Booksop
Location:  Behind The National Theater next to Jafar bookshop.
Tel:.  

ከእንጦጦ እስከ ባሮ በምንሊክ ዘመነ መንግስት በሩሲያዊው እስክንድር ቡላቶቪች በሩሲያ ቋንቋ ተጽፎ በዶር. ኣምባቸው ከበደ ወደ አማርኛ የተመለሰ በጊዜው የነበረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ምድራዊ አቀማመጥን ጨምሮ የሕዝቡን አኗኗር እንዲሁም ባሕልና እምነት የሚተርክ መጽሐፍ ነው።

ከገፅ 110 ከመጽሐፉ የተወሰደ
"በነገራችን ላይ ኦሮሞዎች አንድ አስደናቂ የሆነ ልማድ አላቸው። ይህን ያህል ጠላቶች ገድያለሁ ብሎ መናገር ነውር ስለሆነ የኦሮሞ ወንድ በሕይወት እያለ ይህን ጀግንነት ፈፅሜያለሁ ብሎ አይፎክርም የሓበሾች ልማድ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ሰውየው ከሞተ በኋላ ግን የሟቹ ወንድሞች ወይም ደገኞች፤ ሰውየው መቼ፣ የትና በምን ዓይነት ሁኔታ ምን ዓይነት ጀብዱዎች እንደፈጸመ የመዘርዘር ግዴታ አለባቸው።"

ከገፅ 150 የተወሰደ
"ሸማውን ኣፍንጫው ድረስ ተከናንቦ ዙሪያውን በንቀት እየቃኘ የተቀመጠ ወይም ቀስ ብሎ እየተጎማለለ የሚሄድ ሃበሻ የሚሰማው ኩራት ኩራት አይደለም። ሌላው ታናሽ ከታላቁ ጋር በሚያወራበት ጊዜ በሸማው ጫፍ አፉን መሸፈን አለበት።

 

   
       
 
 
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ


ተመዝግበው ከሆነ እዚህ ይጫኑ

 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com