የኢትዮዽያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
 
     


የታኅሣሡ ግርግርና መዘዙ ደራሲ:(ብርሃኑ አስረስ)
 
ማን ይናገር የነበረ... የታኅሣሡ ግርግርና መዘዙ በሚል ርዕስ አቶ ብርሃኑ አስረስ ያቀረቡልን መጽሐፍ ዋነኛው ትኩረቱ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ላይ ሲሆን ፤ እሳቸው በቦታው ስለነበሩ፣ ተካፋይም ስለሆኑ፣ ያዩትንና የሰሙትን ትውስታቸውን ያቀረቡበት ነው። ይህ መጽሐፍ አያሌ፣ ከዚህ በፊት የማይታወቁ ፣ ኩነቶችን አቅርቦልናል። ከነርሱም መካከል ስለኮሎኔል ወርቅነህ ፣ መፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ እንዲደረግ ምክንያት እንደሆነች በተለያዩ ጸሐፊዎች የተነገረላት ቴሌግራም ጉዳይ እና የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ሲካሔድ በኮ/ል ወርቅነህና በጀነራል መንግሥቱ መካከል ስለነበረው የስልት ልዩነት የገለጹልን ይገኙበታል።

...ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ኮሎኔል ወርቅነህን ከክብር ዘበኛ መኮንንነት አንስተው የልዩ ካቢኔያቸው የደህንነት ሹም ያደረጉት በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. ነበር። ከዚህ ወቅት እስከ መፈንቅለ መንግስቱ ድረስ ያለው ጊዜ አጭር ቢሆንም፣ ወርቅነህ ብዙ ጉዳዮችን ያከናወነበት ወይም ቢያንስ ለውይይት ያነሣሳበት ነበር ማለት ይቻላል። የመሬት ይዞታ ነገር በአእምሮው ውስጥ ይጉላላ እንደነበርና የሪፎርም አስፈላጊነትን አምኖበት እንደነበር ከብርሃኑ ትረካ በግልጽ ማየት ይቻላል።

...ዳራሲው ለወርቅነህ እጅግ በጣም ታማኝ ስለነበሩ ይህም በጣም የሚያስደንቀው ባህርያቸው ነው!፣ አለቃቸው የት እና እንዴት እንደወደቀ ሥራዬ ብለው ተከታትለዋል ለማጣራት ሞክረዋል። ገለጻቸው፣ ሌሎቹ ባጭሩ ያቀረቡትን ምስክርነት አስፋፍቶ ያቀርባል፤ የተሻለም ተአማኒነት አለው፤ ስለዚህ፣ ስለኮሎኔል አሟሟት ከአሁን በሁዋላ እርግጠኛ ሆኖ መጻፍም ሆነ ማውራት ይቻላል።

... መፈንቅለ መንግሥቱ ውስጥ በመካፈላቸው ለአያሌ አመታት ታሥረው ከተፈቱ በሁዋላ፣ አቶ ብርሃኑ ጉዳዩን ሲከታተሉ ቴሌግራሟን አግኝተዋት ኖሮ፣ በመጸሐፋቸው ውስጥ የፎቶ ግልባጭ ከተዋል፤ በትረካቸውም ውስጥ ይጠቅሷታል። ለመጀመሪያ ጊዜ አንባቢም ያያታል፤ ይልቁንም ዘመኑን የሚያጤኑ የታሪክ ጸሐፊዎች ቀረብ አድርገው እንደሚያተኩሩባት አይጠረጠርም።

...የወርቅነህ ሐሳብ በአስቸኳይ አንድ መቺ ኃይል ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ኮማንዶ ፖስት መሿለኪያ አጠገብ ሔዶ፣ አዚያ ያሉትን ጀነራሎች ቢቻል መያዝ፣ ካልተቻለ መደምሰስ አለበት የሚል ነበር። ይህንን የኮማንዶ ኦፕሬሽንም ካስፈለገ ራሱ ለመምራት ዝግጁ እንደሆነም ገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ ጄኔራል መንግስቱ በማያወላዳ ምክንያት፣ አልተቀበለውም፤ ጉዳዩም በዚህ ተዘጋ። ይህ አለመግባባት ወርቅነህ ጎበዝ፣ ፈጣንና ብሩህ አእምሮ የነበረው ሰው እንደነበረ ፍንትው አድርጎ አሳያል። ስለእሱ ተክለ ሰውነትና ችሎታ ዘመነኞቹ ይሉት የነበረውን ሁሉ የሚደግፍ ይሆናል፤ እውነትም፣ ወርቅነህ ቀላል ሰው አልነበረም፤ እውነትም፣ አፄ ኃይለሥላሴ ሰው መምረጥ ያውቃሉ የሚያሰኝ ነው።

ባጭሩ፣ ይህ ሥራ የ፳ኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያን የፖለቲካና የማህበራዊ ታሪክ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች በእጅጉ ሊጠቀሙበት የሚችሉት መጽሐፍ ነው።

ሺፈራው በቀለ
የኢትዮጵያ ታሪክ ፕሮፌሰር
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
 
 
 
 
ስለመጽሐፉ የአንባብያን አስተያየት።       

መጽሐፉን አንብበውት ከሆነ ስለመጽሐፉ ያለዎትን አስተያየት ይጻፉ።
If you have already read the book, please write your review or comment.

ስም /Name: *
ኢሜይል /Email: *
አስተያየት/
Your book review:
*
   
Dear Readers: The views expressed on our comment section below are the personal views of individual contributors and ethireaders.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that Comments are moderated if necessory.
 
 
 
 
   
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com