ይህ በኒዘርላንድ ናኖ ሕትመትን በመጠቀም ሊሠራ የታሰበው የብረት ድልድይ የኮምፒዩተር ምስል ነው። ሁለቱ ሮቦቶች ከየወገናቸው የብረት ድልድዩን ካለደጋፊና መወጣጫ እያተሙ ሁለቱም ያጠናቅቁ
የድልድዩ ሁለት ወገኖች ይገጥማሉ። በዚህ በፎቤስ መጽሔት በናንሲ አዋኖ በቀረበ ጽሑፍ በ2008 (20017 እኤአ) የደች መሃንዲስ ላርማን ሁለቱን ሮቦቶች በካናሉ ላይ አድርጎ ካስነሳ በኋላ በሁለት ወሩ ተመልሶ ሲመጣ የሰው መሸጋገሪያ ድልድዩ ተገባዶ ለመገልገያነት ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል።