እኔና አሴ ላለፉት 56 አመታት በደጉም ሆነ በክፉ ገጠመኞች፤ በወንድማማችነትና በወዳጅነት፤ በፍቅርና በመተሳሰብ ኖረናል። በ1952 ያለፉ ፈተናዎችና ጥያቄዎች አደን ነበር ያገናኘን።ዲላና ሻሸመኔ የጋሞ፤ የዎላይታና የጉራጌ መናሐሪያዎች ስለሆኑ ያስተዋወቁኝ የጋሞ ወይም የዎላይታ ተማሪዎች ናቸው። ከዲላ ወደ ቫሸመኔ መጥቼ ከአሴ የነበረ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ጥያቄዎች ሰብስቤ ወደ ዲላ ተመለስኩ። ሁለታችንም የስምንተኛን ክፍል ፈተና በከፍተኛ ውጤት አልፈን አዲስ አበባ ኮከብ ጽባሕ መምህራን ማሰልጠኛ ተመደብን። አሴ ሲቪል አቪዬሽን እስከ ገባበት አንድ ቤት ተከራይተን እንኖር ነበር።
አሴን በትዝታ ፈለግ ውስጥ እንደገና ስለ አገኘሁት ተደስቻለሁ። በ28 ምእራፎች የተከሸነ የትዝታ ፈለግ በቃላት የተሳለ ውብ ስዕል ነው።
ግርማ ይልማ የኢሕድሪ የማስታወቂያ፤ የባህል ሚኒስቴር፤ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር |