ከመጽሐፉ የተወሰደ
ሕብረት ባጣ የኃላፊነት ሥራ ለሹመት፣ለመወደድ ሲባል በሚደረግ ሩጫ መካከል ሰሚ የሚያጡ ማህበራዊ ችግሮች እየተደመሩ የሕዝብ እሮሮና ጩኸቶች እየበረከቱ፣ በደሎች እየወፈሩን እየሰፉ፣ እድገታቸውም ተመንድጎ እየወጣ መመለሻና መቃኛ ከሌለው ችግር ውስጥ ተዘፍቀው ይቀራሉ። ጦሳቸውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ተላላፊ በሽታ ይሆናል።
አገርን ለመምራት የታደሉና የተመረጡ መሪዎችና ሹሞች አልሚነትና አጥፊነታቸውን ሕዝብን መስተዋታቸው አድርገው እራሳቸውን መመልከት ቢችሉ፣ ሕዝብ በመስተዋትነቱ ከእምነት ስለማይርቅባቸው አገር መልጽጋ ፣ ፍትህና ርትዕ ነግሦ፣ የአገር መሬት ፍሬዋን ሰጥታ መክበሪያና መጠቀሚያ እንጂ መቀበሪያ ብቻሆና ዜጎቿን አታስተናግድም።
ስለ መጽሐፉ የቀረበውን ሙሉ ቅኝት ለማንበብ እዚህ ይጫኑ