|
|
በለጠ ገብሬ |
|
|
|
|
|
በሪሁን ከበደ |
|
|
|
|
|
[1930 - 1976] |
|
በአሉ ግርማ |
በዓሉ ግርማ በቀድሞ አጠራሩ በኢሊባቦር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዘነበወርቅ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጀኔራል ዊንጌት አጠናቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በፖለቲካል ሳይንስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ፡፡ ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶች መካከል በ፲፱፷፪ ዓ.ም. የታተመው "ከአድማስ ባሻገር" የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩሲያ ቋንቋ ተተርጉሞ ለቀድሞዋ ሶቪየት ኀብረት አንባቢያን ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ ነበሩ፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ፣ የመነን መጽሔት፣ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔትና የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሠርተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት ይታተም የነበረው አዲስ ሪፖርት የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃም እንዲገመገም አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮም በኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ በዓሉ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን የሠሩ ደራሲ ናቸው፡፡ የመጨረሻው መጽሐፋቸው "ኦሮማይ" በወቅቱ በነበረው መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ፲፱፸፮ ዓ.ም. ለሕይወታቸው መጥፋት መንስኤ ሆኗል፡፡ በዓሉ ካሳተሟቸው መጽሐፍት መካከል "የሕሊና ደወል" "የቀይ ኮከብ ጥሪ" በ፲፱፷፮ ዓ.ም. እና "ሐዲስ" በ፲፱፸፪ ዓ.ም. ይገኙበታል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|
በዓሉ ግርማ በቀድሞ አጠራሩ በኢሊባቦር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዘነበወርቅ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጀኔራል ዊንጌት አጠናቀዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በፖለቲካል ሳይንስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። |
|
|
|
|
|
በቀለ ተገኝ |
|
|
|
|
|
[1920 - 1948] |
|
በላይ ግደይ |
በላይ ግደይ በቀድሞው ትግራይ ክ/ሀገር መጋቢት 7 ቀን በ1920 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በተወለዱበት ሥፍራ ፊደል ከቆጠሩ በኋላ በ1937 ዓ.ም. አ.አ. ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተማሩ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡ በተጨማሪም በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በማታው የትምህርት መርሐ ግብር የከፍተኛ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን በውጭ ሀገርም የባንክ አገልግሎት ሥራ ተምረዋል፡፡
በላይ ግደይ “ገንዘብ፣ ባንክና መድን በኢትዮጵያ”፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ”፣ “ቅድስት አክሱም”፣ በሚሉ ርዕሶች መጽሐፎችን በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተውና አሳትመው ለአንባብያን ያቀረቡ ሲሆን፣ “Currency ad Banking in Ethiopia”፣ “Ethiopian Civilization” በሚሉ ርዕሶችም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽፈው ያዘጋጇቸውና ያሳተሙዋቸው መጻሕፍትም አሏቸው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|
በላይ ግደይ በቀድሞው ትግራይ ክ/ሀገር መጋቢት 7 ቀን በ1920 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በተወለዱበት ሥፍራ ፊደል ከቆጠሩ በኋላ በ1937 ዓ.ም. አ.አ. ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተማሩ። |
|
|
|
|
|
በቀለ ሰጉ |
|
|
|
|
|
በቀለ ወ/ማርያም አዴሎ |
|
|
|
|
|
በረከት ስምኦን |
|
|
|
|
|
በቀለ መኮንን |
|
|
|
|
|
በድሉ ዋቅጅራ |
|
|
|
|
|
በዕውቀቱ ሥዩም |
|
|
|
|
|
በእምነት ገብረአምላክ |
በእምነት የተወለዱት በ፲፱፲፫ ዓ.ም. ነበር፡፡ በኤርትራ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት በእምነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በስዊድን የሚሲዮን ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን መከታተል ቢጀምሩም በጣሊያን ወረራ ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡ ቀጥሎም ጣሊያን ኮንስላታ ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለው በቤተሰብ ችግር ምክንያት አቋርጠዋል፡፡ ለጣሊያኖች በፎቶግራፍ አንሺነት ተቀጥረው ሰርተዋል፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ በኃይል ተሸንፎ ከተባረረ በኋላ በፖሊስ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት ለስድስት ዓመታት አገልግዋል፡፡ ወደ አሜሪካ በመሄድ ትምህርት መማር ቢጀምሩም በአየር አለመስማማት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል በ፲፱፶፰ ዓ.ም. በቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በማዕረግ ተመረቁ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የማስተማር ዕድል አጋጥሟቸው በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ለመሥራት አሜሪካ የሄዱ ቢሆንም ነገር ግን የቤተሰብ ችግር ስላጋጠማቸው ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ለመመለስ ተገደዋል፡፡
ለአማርኛ ቋንቋ ማደግ ይከራከሩ የነበሩት በእምነት የተለያዩ የትርጉም ሥራዎች ቢኖሯቸውም በእጅጉ የሚታወቁት ግን “ልጅነት ተመልሶ አይመጣም” በሚለው ተወዳጅ ድርሰታቸው ነው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ካሌንደር። |
በእምነት የተወለዱት በ፲፱፲፫ ዓ.ም. ነበር፡፡ በኤርትራ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት በእምነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። |
|
|
|
|
|
ዶ/ር ባሕሩ ዘውዴ |
|
|
|
|
|
ባይሩ ታፍላ |
|
|
|
|
|
ባሴ ሀብቴ |
|
|
|
|
|
ባቢሌ ቶላ |
|
|
|
|
|
ቤካ ነሞ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ አስረስ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ድንቄ |
|
|
|
|
|
[1925 - 1979] |
|
ብርሃኑ ዘርይሁን |
ብርሃኑ ዘርይሁን በ1925 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ይገኝ በነበረው በቀድሞው ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ትምህርትቤት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በተግባረ እድ ትምህርት ቤት በሬዲዮ ቴክኒሺያንነት ሙያ ተመረቁ።
ሥራ የጀመሩትም በመምህርነት ነው። በወቅቱ በካርታ ሥራ ድርጅት ቴክኒሺያንነት ሙያ ሠርተዋል። ከዚያም የጦር ሚኒስቴር እየተባለ ይጠራ በነበረው የአሁኑ መከላከያ ሚኒስትር በአስተርጓሚነት አገልግሏል። ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዲዛወሩ ከተደረገ በኋላ የኢትጵያ ድምጽ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነዋል። ከሶስት አመት በኋላ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው የማይረሳ ተግባር አከናውነዋል።
ብርሃኑ ዘርይሁን የደረሱት ‹ሞረሽ› በ1972 ዓ.ም፤ ‹ጣጠኛው ተዋናይ›በ1975 ዓ.ም እና ‹አባደፋር› በ1977 ዓ.ም፤ የተባሉት ቴያትሮቻቸው ተወዳጅ ነበሩ።
ከጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥም ‹የቴዎድሮሥ እንባ › በ1958 ዓ.ም፤ ‹የእንባ ደብዳቤዎች› በ1961 ዓ.ም እና የታንጉት ምሥጢር› በ1978 ዓ.ም፤ እንዲሁም ለረጅም ተከታታይ ጊዜያት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሲተረኩ የነበሩት ‹የአብዮት ዋዜማ፤የአብት መባቻና የአብዮት ማግስት› የተሰኙት ማጸሐፍት ይገኙበታለል።
ብርሃኑ ዘርይሁን ለሐገራቸው የስነ ጽሁፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አበርክተዋል። በቀዳሚዎቹ ዘመናት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርን በሥራ አመራር አባልነት ካገለገሉት መካከል አንዱ ብርሃኑ ናቸው።
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |
ብርሃኑ ዘርይሁን በ1925 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ይገኝ በነበረው በቀድሞው ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ትምህርትቤት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በተግባረ እድ ትምህርት ቤት በሬዲዮ ቴክኒሺያንነት ሙያ ተመረቁ። |
|
|
|
|
|
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ |
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ በሸዋ ክፍለ ሀገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በ፲፱፳፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜም ትምህርታቸውን በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተል ከየንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ጥቅምት ፲፱፳፫ ዓ.ም. በወታደርነት ተቀጥረው ለአሥር ዓመታት፤ በሲቪል ፀሐፊነት ደግሞ ለሃያ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከ፲፱፶፫ ዓ.ም. ጀምሮ ድርሰት መጻፍ የጀመሩት ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል “ፈላስፋው ቃየል ነው”፣ “እሬትና ማር”፣ “የድሆች ጠበቃ”፣ “ዳኞች በፍርድ ላይ”፣ “ባሌ መታኝ አለች ወይስ ፈታኝ” የሚባሉት የገኙበታል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ በሸዋ ክፍለ ሀገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በ፲፱፳፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜም ትምህርታቸውን በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተል ከየንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል። |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ አበበ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ንጉሤ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ለሜሳ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ አባዲ |
|
|
|
|
|
ብስራት አማረ |
|
|
|
|
|
ብአዴን |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ነጋ |
|
|
|
|
|
ቦጋለ ተፈሪ በዙ |
|
|
|
|