ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ብላታ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ
[1889 - 1974]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የወንድ ልጅ ኩራት ፥ ስለሀገር መሞት(ግጥምና ቅኔ)
2.   የዓለም ጠባይ ፥ ሐሴትና ብካይ(ግጥምና ቅኔ)
3.   አግዐዚ(ልብወለድ)
4.   ከሥራ: በኋላ : ሥራ : ስትፈቱ : እንቆቅልሽ : ተጫወቱ።(ወግ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በሸዋ ክፍለ ሀገር በምንጃር ወረዳ በ፲፰፹፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ በአካባቢያቸው ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ከተማሩ በኋላ በሸዋ፣ በወሎና በጎንደር እየተዘዋወሩ ለአሥራ ስድስት ዓመታት ያህል የፀዋትወ ዜማ የቅኔና የመጻሕፍት ትርጉም ትምህርት ተከታትው አጠናቀዋል።

ብላታ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር በመሆን መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተርጉመዋል፡፡ በ፲፱፲፬ ዓ.ም. ቤተ ሳይዳ ይባል የነበረው ጋዜጣ ሲቋቋም ምክትል አዘጋጅ በመሆን ሠርተዋል፡፡ ብርሃንና ሰላም ጋዜጣና ከሣቴ ብርሃን ለልብ ጠቢባን ይባል የነበረው መጽሔት ዝግጅት አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ በኋላም የሰንደቅ ዓላማችንና የአዲስ ዘመን ዋና አዘጋጅ በመሆን ሠርተዋል፡፡ እንዲሁም በኃላፊነት በዲሬክተርነትና በረዳት ሚኒስትርነት፣ የማስታወቂያ ሚኒስቴር አማካሪ በመሆን ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com