ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አለማየሁ ሞገስ
የደራሲው ሥራዎች
1.   መልክዐ አትዮጵያ(ግጥምና ቅኔ)
2.   አንድ መንጋ ፥ አንድ እረኛ(መልክ፥ ገድልና:ነገረ:መለኮት)
3.   ሁሉም ሁሉን ይወቅ(መልክ፥ ገድልና:ነገረ:መለኮት)
4.   ለምን አልሰለምሁም(መልክ፥ ገድልና:ነገረ:መለኮት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ዓለማየሁ ሞገስ በ፲፱፲፰ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ባህላዊ ትምህርት ቤት ገብተው ዜማ ተማሩ፡፡ ጣሊያን ሀገራችንን በወረረች ጊዜ የአርበኝነት ግጥም እየገጠሙ የአርበኞችን ወኔ ይቀሰቅሱ ነበር። የግዕዝን ዐዋጅ አገባብና የቅኔን ሥርዓት በአጭር ጊዜ የተማሩት በግላቸው ጥረት በቤት ውስጥ ነበር። ከዚያም በ፲፱፴፮ ዓ.ም. በቅኔ መምህርነት ተመረቁ፡፡ በ፲፱፴፰ ዓ.ም. ዘመናዊ ትምህርት ጀመሩ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና በታሪክ ሁለት የቢ.ኤ.ዲግሪና በኢጣሊያን አገር የሥነ ጽሑፍ ዲግሪ አግኝተዋል። በተጨማሪም ግዕዝ፣ ትግርኛ፣ ግሪክ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ ያውቃሉ። ላቲን ዐረብኛና ቱርክ ያነባሉ። አብዛኞቹ መጻሕፍታቸው በግዕዝ ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ ሲሆን በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የጻፏቸውም ድርሰቶች ቁጥር በርካታ ናቸው።

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com