ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
መስፍን ዓለማየሁ ጠይቃቸው
የደራሲው ሥራዎች
1.   የቴዎድሮስ ዕንባ(ተውኔት)
2.   ካፖርቱ( ትርጉም)
3.   ሽማግሌውና ባሕሩ( ትርጉም)

ስለደራሲው በጥቂቱ
መስፍን ዓለማየሁ በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ጅጅጋ ከተማ መስከረም ፳፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09#9 ዓ.ም.፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ09%1 ዓ.ም. አጠናቀቁ።

መስፍን ዓለማየሁ “የቴዎድሮስ ዕንባ”፣ “የቬኑሱ ነጋዴ”፣ የተሰኙ ተውኔቶችን “የሽዋስቲካ ምሥጢር”፣ “ካፖርቱ”፣“የመጨረሻዋ ቅጠል”፣ “ሽማግሌውና ባሕሩ”፣ በመባል የሚታወቁ ልቦለድ የትርጉም መጻሕፍት አሳትመው ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ግጥሞች፣ አጫጭር ልቦለዶች፣ በጋዜጦች፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለሕዝብ አቅርበዋል፡፡

መስፍን ዓለማየሁ በሕይወት ዘመናቸው በቀድሞዋ ሶቪየት ኀብረት በሞስኮ 12ኛው የወጣቶች ፌስቲቫል በተከበረበት ወቅት በሶቭየት ደራስያን ማኀበር አዳራሽ በተካሄዱ የሥነ ጽሑፍ - ጉባኤዎች ላይ ማኀበራችንን ወክለው ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com