ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ብላታ መርስዔ ሐዘን ወልደ ቂርቆስ
[1891 - 1971]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ(ታሪክ)
2.   ዐውደ መዋእል(ታሪክ)
3.   የትእምርተ መንግሥት ታሪክ በመዋዕሊሁ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ(ታሪክ)
4.   የኢትዮጵያ መዝገበ ቃላት(ቋንቋ)
5.   ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጎንደርን የመጎብኘታቸው ታሪክ ፲፱፻፴፱ መስከረም ፳፫ - ጥቅምት ፯።(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
መርስዔ ኀዘን ወልደቂርቆስ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል አካባቢ በ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተወለዱ። ትምህርት የጀመሩት በልጅነታቸው ሲሆን በጊዜው ዳዊት ደግመዋል፡፡ ከዚያም የዜማ ትምህርት በመጀመር ጾመ ድጓና ድጓ አስኪደዋል፡፡ ቀጥሎም ቅኔ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ፲፱፻፭ ዓ.ም. የመጀመሪያ ሥራቸውን የወንበር ፀሐፊ በመሆን እየሠሩ አገልግለዋል፡፡ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን፣ የዮሐንስ አፈወርቅን ትርጓሜ፣ እንዲሁም የመቅድመ ወንጌልን ትርጓሜ ትምህትን አጠናቀዋል፡፡ እኝህ ታላቅ ሰው ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ሲመሠረት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ፣ ቀጥለውም የተፈሪ መኮንን ት/ቤት የግዕዝና የአማርኛ አስተማሪ በመሆን ሠርተዋል፡፡ እንዲሁም ከ፲፱፴፫ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፷፫ ዓ.ም. ድረስ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ ኃላፊነቶችና በዲሬክተር ማዕረግ ሠርተዋል፡፡ ሥነ ጽሑፍንና ታሪክን በተመለከተ አሥራ ሦስት መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ሰባት መጻሕፍትን ተርጉመዋል፡፡ የተለያዩ ጽሑፎችን አሰባስበው አዘጋጅተዋል፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥራዎችን ከሊቃውንት ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል፡፡ የአማርኛ ስዋስው መጽሐፍ ባለመዘጋጀቱ ተማሪዎች ተገቢውን የቋንቋ ትምህርት ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን በማየትም በ፲፱፴፭ ዓ.ም. “የአማርኛ ስዋስው” የተባለ መጽሐፍ አዘጋጅተው በማቅረብ ችግሩ እንዲቃለል አድርገዋል። መርስዔ ኀዘን በላቀ የሥነ ጽሑፍ ሥራቸው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት ተሸላሚ ናቸው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com