|
|
[1909 - 1991] |
|
ዶ/ር ከበደ ሚካኤል |
ባለታሪኩ ከበደ ሚካኤል ጥቅምት 23 ቀን 1909 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ -- ደብረ ብርሃን ከተማ አካባቢ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ተወለዱ።
በህፃንነታቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ልዩ ልዩ ታሪኮች በወግ መልክ በመተረክ እንደ አነፅዋቸው የመሰከሩላቸው እናታቸው ወ/ሮ አፀደ ሚካኤል ጀንዲ እስከ ዘጠነኛ አመታቸው ድረስ በባህላዊን የግዕዝ ትምህርት እንዲቀስሙ እንዳስቻሏቸው ይነገራል። ከበደ በ1918 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በእናታቸው ወንድም በአቶ ሰይፉ ሚካኤል ልዩ ድጋፍ በ"አሊያንስ ፍራንሴስ" በፈረንሣይኛ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን፥ በላዛሪስ ሚሲዮንም የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
ከበደ ሚካኤል እስከ ጣሊያን ወረራ ዋዜማ ድረስ በነበረው የተማሪነት እና የወጣትነት ቆይታቸው ከመደበኛ ትምህርታቸው ባሻገር በትርፍ ጊዜያቸው ልዩ ልዩ የፈረንሳይኛ መጸሐፍትን በማንበብ የቋንቋ የንግግር ችሎታቸውን አዳብረዋል። አንድም - በዘመናቸው ከነበሩት ቀደምት ታዋቂ ኢትዮዽያውያን ምሁራን - የአለቃ አፅመ ጊዮርጊስን፥ የአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌን፥ የፕሮፌሰር አፈወርቅ ገ/ኢየሱስን፥ የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝን እና የነቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴን አዳዲስ ሓሳቦች ቀስመዋል። ከትምህርት ቤት መምህራኖቻቸው ይሰጡዋቸው በነበረ ልዩ ድጋፎችም የግሪክን የሮማውያንን፥ የእንግሊዝን፥ የፈረንሳይን፥ የጀርመንን፥ የሩሲያን እና የኢታሊያን ፈላስፎች ጠቢባንና ሳይንቲስቶች "ታላላቅ ሰዎች" መጻህፍት አንብበዋል መርምረዋል።
ከኢጣሊያ ወረራ 1929 -1933 ዓ.ም በኋላ በ"ነፃነት መዝሙር" -የቅኔ መንገድ ልዩ ተሰጥኦዋቸውን አሀዱ ያሉት ከበደ ሚካኤል ከሃገራችን ደራሲያን በላቀ መልኩ በዘመናዊ እሳቤና ሥነ ጽሑፋዊ ተሳትፎአቸው ከ16 በላይ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ የእውቀት ዘርፎች ፍልስፍና፥ ሥነመለኮት፥ ሥነ ትምህርት፥ ሥነምግባር፥ ሳይንስ፥ ሥነ ጥበባት፥ ቅኔ፥ ተውኔት "ብርሀነ ህሊና" በብእሮቻቸው መግለጫነት በአማርኛ፥ በፈረንሳይኛ፥ በእንግሊዝኛ፥ እና በጣሊያንኛ ቋንቋዎች ከ90 በላይ በታተሙ ከ200 በላይ ባልታተሙ ወጥና ትርጉም ድርሰቶቻቸው የኢትዮዽያን ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ አድማስ አስፍተዋል።
በአዳዲስ ሀሳቦች "አብራሄ ህሊና"ነት ሀዲስ ትውልድ ያፈሩት ፈላስማውና ባለቅኔው ከበደ ሚካኤል፥ ዘመናዊ ኢትዮዽያን ለማደራጀት በተደረገው ተጋድሎም በልዩ ልዩ የሚኒስትርነት ማእረጎች በግምባር ቀደምነት አገልግለዋል።
ፈላስፋ፥ ባለቅኔ፥ ፀሐፊ ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋው ጋዜጠኛ ከበደ ሚካኤል በአገራችን እንግዳና የመጀመሪያ የነበረውን የቀ.ኃ.ሥ. የ1957 ዓ.ም የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በቀዳሚነት የተቀበሉ የ"ቀለም ሰው" ሲሆኑ፥ በዘላቂነት ሐዲስ ትውልድ ላፈራው የላቀ አስተዋፀኦዋቸውም የአ.አ.ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 26 ቀን 1990 ዓ.ም በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል።
ክቡር ደ/ር ከበደ ሚካኤል ኅዳር 3 ቀን 1991 ዓ.ም በ82 ዓመታቸው አረፉ። "ሰኔ 21 ቀን የከበደ ሚካኤል መታሰቢያ ቀን" ሆኖ ተሰይሟል።
ምንጭ:ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር። |
ባለታሪኩ ከበደ ሚካኤል ጥቅምት 23 ቀን 1909 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ -- ደብረ ብርሃን ከተማ አካባቢ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ተወለዱ። |
|
|
|
|
|
ከበደ ደስታ |
|
|
|
|
|
ደጃዝማች ከበደ ተሰማ |
|
|
|
|
|
ከበደ እንግዳው |
|
|
|
|
|
ከፍያለው መራሒ |
|
|
|
|
|
ከበደ ደበሌ ሮቢ |
ከበደ ደበሌ በአርሲ ክፍለ ሀገር ጭላሎ አውራጃ ኀዳር ፩፮ ቀን ፲፱፶፭ ዓ.ም. ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሳጉሬ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ አጠናቅቀዋል፡፡ በተጨማሪም የጋዜጠኝነትና የጦር ምህንድስና ትምህርት ተከታትለዋል፡፡
ከበደ ደበሌ “ጥምር ፍቅር”፣ “ቁርሾ”፣ “ሽብልቅ”፣ “ጎርፍ”፣ በመባል የሚታወቁ ልቦለድ መጽሐፎችን ለኀትመት አብቅተዋል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |
ከበደ ደበሌ በአርሲ ክፍለ ሀገር ጭላሎ አውራጃ ኀዳር ፩፮ ቀን ፲፱፶፭ ዓ.ም. ተወለዱ። |
|
|
|
|
|
[1862 - 1936] |
|
አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ |
ይኼ:ሰው:ባ፲፰፻፹፪:ዓ.ም. እንደሳቸው:እንደ:ራሳቸው : ጥበብን : ከምንጩ : ለመጠጣት : ወደኢየሩሳሌም : የዘለቀው : የ፳ : ዓመቱ : የወንዛቸው : ልጅ : ኪዳነወልድ : ነበር፡፡ ዘመኑም : እሳቸው : ከሮሜ : በተመለሱ : በኹለተኛው : ዓመት : ኪዳነወልድ : ካገር : በወጣ : በዘጠነኛው : ዓመት : ባ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተመልሰው : ወዳገራቸው : መጡ፣ መቼም : ተደርጎ : በማያውቅ : ኹኔታ : የሕዝቅኤልን : ረቂቅና : ጥልቅ : ያንድምታ : ትርጓሜ : ባ፲፰፻፲፮ ዓ.ም. ድሬዳዋ : ላይ : አሳትመው : አስረከቡ፡፡ በምላሹ : ይህ : ደብዳቤ : ተጽፎላቸው : ነበር።
የኢትዮጵያ : መንግሥት : ዐልጋ : ወራሽና : እንደራሴ : ተፈሪ : መኰንን
ይድረስ : ካቶ : ኪዳነወልድ፤
እንደምን : ሰንብተሃል : እኔ : እግዚአብሔር : ይመስገን : ደኀና : ነኝ፡፡ ስለሕዝቅኤል : ትርጓሜ : የላክኸውን : መጽሐፉንም : ደብዳቤውንም : አይቼዋለሁ፡፡ ነገር : ግን : ቃለ : በረከትና : ሙባአ : ብለህ : በራስህ : አሳብ : የጻፍከው : ቃል : ከኢትዮጵያ : ታሪክና : ከሊቃውንቱ : ልማድ : የተለየ : ስለኾነ : ወሬውን : ለሚሰሙ : ሊቃውንቶች : የሚያሳዝን : መጽሐፉንም : ለሚያነቡ : ሰዎች : ኹሉ : የነቀፋ : ምክንያት : የሚኾናቸው : ይመስላልና : ዐብሮ : ለመጠረዝ : አያስፈልግም፡፡ መቸም : እኛ : የፈለግነው : ያንኑ : ጠፍቷል : የተባለውን : የነቢዩን : የሕዝቅኤልን : ትርጓሜ : ለየሰው : ኹሉ : ለመግለጽና : ደስ : ለማሰኘት : እንጂ : በዚህ : በትርፍና : በትንሹ : ነገር : መጽሐፉን : ለማስነቀፍ : ምክንያት : የሚኾን : ነገር : ለመጻፍ : ያስፈልግም፡፡
የውጭ : አገር : ታሪክ : ጸሐፊዎች : እንኳ : የብሉይ : መጻሕፍት : በኢትዮጵያ : ቋንቋ : እንደተገለበጡ : ጽፈዋልና : አኹን : አንተ : የብሉይ : መጽሐፍት : ወደ : ኢትዮጵያ : ቋንቋ : አልተገለበጡም : ብለህ : ብትጽፍ : ለሀገራችን : ክብር : አይኾንም፡፡ ለማናቸውም : ቢኾን : የራስህ : ሐሳብ : ነው : እንጂ : የነቢዩ : የሕዝቅኤል : ቃል : አይደለምና : ቢቀር : ይሻላል፡፡
የሚቀረውም : በቀይ : ቀለም : ተሠርዞ : ተመልክቷልና : እንደተሠረዘ : ማድረግ : ነው፡፡ ከመጽሐፉም : ጋር : ዐብሮ : የሚታተመውን : የኔን : ፎቶግራፍ : ልኬልሃለሁ፡፡
ጥር : ፴ : ቀን : ፲፱፻፲፮ : ዓመተ : ምሕረት : ዐዲስ : አበባ፡፡
ለማንኛውም : ኪዳነወልድ : ባልጠበቁት : መልኩም : ቢኾን : መጽሐፉ : ታትሞ : ሕዝብ : እጅ : ገብቷል፡፡
ታምራት : አማኑኤል : ስለ : ኢትዮጵያ : ደራሲያን : በሚለው : ጥሑፋቸው : ስለኪዳነወልድ : ትርጉም : እንዲህ : ብለዋል፡-
… በኢትዮጵያ : መጻሕፍት : ካላቸው : ከሰፊው : ዕውቀታቸው : በላይ : ላገራችን : መጻሕፍት : መሥጢርና Sens : ታሪክ : አስፈላጊ : የኾነውን : የመጽሐፍ : ቅዱስን : ዕብራይስጥ : ጨምረውበታል፡፡ የሕዝቅኤልን : ትንቢት : ዕብራይስጡን : ወዳማርኛ : ገልብጠው : ባማርኛ : የጨመሩበት : መግለጫ፤ ከኹሉ : በፊት : ላገራችን : ሊቃውንት : ከግሪክ : ተተርጉሞ : በግእዝ : ተቀብለውት : የሚኖሩትን : የብሉያትን : መጻሕፍት : ዋናውን : አብነት : ዕብራይስጡን : እያዩ : ማቃናት፣ እንዳለባቸው : አነቃቅተዋቸዋል፡፡ ዳግመግኛ : ትምህርቱም : መጠነኛ : ቢኾን : ዐማርኛ : ያወቀ : ኹሉ : ሊያስተውለሉና : ሊያጣጥመው : በሚችል : ንግግር : በመግለጣዠው : ተራውን : ሕዝብ : ሳይቀር : ከሊቃውንቱ : ዕውቀት : እንዲካፈል : አድርገውታል፡፡ እግረ : መንገዳቸውንም : ልዩ : ለኾነው : ከባድ : ዕውቀት : ልዩ : የኾነና : ያጌጠ : ዐማርኛ : ፈጥረውለታል …
ዜማ : ለመማር : ከደብረ : ሊባኖስ : ወዳዲስ : ዐበባ : ያቀና : አንድ : ዲያቆን : በኾነ : አጋጣሚ : ለብላቴን : ጌታ : ኀሩይ : ቅኔ : ይቀኛል፤ ኀሩይ : ይደነቁና …
… እንዴ፣ እንዴ : አንተ : ትፈለጋለህ : ለሥራ፤ መቼ : ሥራ : ትፈልጋለህ? … ምን : ሥራ : ነው : የምትፈልገው?
… ማተሚያ : ቤት፡፡ … ነገ : አስገባኻለሁ፤ ግዴለኸም : አሉኝ፡፡ ማንንም : ያኑበታል፤ በጃንሆይ : በገንዘቡም : በኹሉም : ሥልጣን : አላቸው፡፡ … ገብቶ : ይሥራ : ቀለቡን : እንደሰዎቹ : እንደባልንጀሮቹ : እቆርጥለታለሁ : ብለዋል፤ ዐልጋወራሽ : የሚል : ወረቀት : ሰጡኝና : ኼዱ፡፡ በዚየው : ዓመት : ተያኔው : ተፈሪ : መኮንን : ማተሚያ : ቤት : ታኹኑ : ብርሃንና : ሰላም : በተራ : ሠራተኛነት - በሰባት : ጥሬ : ብር : ተቀጠረ፤ እዚያም : ተአለቃ : ኪዳነወልድ : ተገናኘ፡፡ … የማነህ : አሉኝ : ንባብ : ሳነብ : አዩኝና … የታተመውን : የሕዝቅኤል : ትርጉም : ለማስረከብ : ነበር : የኪዳነወልድ : አመጣጣቸው፡፡ የታተመ : ወንጌል : ዲያቆኑ : ያነባል : አለቃ : ዳኜ : ያርማሉ : ያቃናሉ፡፡ ኪዳነወልድ : ገብተው : ቁጭ : ብለው : ካዩ : በኋላ ፡- እናንተ : እግዚአብሔር : ረድቷችኋል፣ እሱ : ያውቃል፣ ርስዎ : ያውቃሉ : ደኀና : ትሠራላችሁ፡፡ እኔ : እዚያ : ጃንሆይ፤ እዚያ : አሳትም : ብለውኝ : እንኳን : ግእዝ : ዐማርኛ : አያውቁም : ካቶሊክ : ተማሪ : ቤት፡፡ እያጨማለቁ : እያጠፉ : ድካም : በድካም : ሹሙንም : እኔንም : በድካም : ገደሉኝ : ደከመን : ሰው : የለም : እዚያ፡፡
ዲያቆኑ፡ ተከተለና ፡- … እነወይዘሮ : በላይነሽ፣ ብላታ : አሸኔ : ደኀና : ናቸው : ወይ : አልዃቸው፡፡ መጠየቁ : ነው፡፡ … ታውቃቸዋለህ? አሉኝ፡፡ … አዎ፤ እነሱ : ቤት : ነው : ያለኹት፤ የነሱ : ነኝ፡፡ … እንዴ፤ የነሱ : ነኽ? … አዎ!
… ለኔም : ያሉኝ : እነሱ : ናቸው : የሚመግቡኝ፣ ለካ : የነሱ : ኖረኻል? እንግዲያ : እኔ : ልውሰድህ : ከኒ : ጋራ : እንኺድ፤ ድሬደዋ : እኔ : ልውሰድህ፡፡ ይኸው : አኹን : እዚህ : መጽሐፉን : አበላሽተውብኝ294 : እንደገና : ይሄ : የተበላሸው : እንደ : ገና : ይሄ : የታተመው : ቀርቶ : ሌላ : ሦስቱን …295 ጃንሆይ : ሰጥተውኛል : አኹን : አስረክበውኛል፤ ‘ዐደራህን : እንደሚያስፈልግ : አርገህ : ዐትምልኝ፤ እኔ : ሊቃውንቱንም : አድክሜ : እኔም : ወጪ : አድርጌ : ተጫወቱበት፤ ሥራውን : የማያውቁት : ሰዎች’ ብለውኛልና : እኔ : ልውሰድህ : አሉኝ፡፡
የዛኔ : ቁርኝቱ : ተዠመረ … ለዲያቆኑ : ዐዲስ : የሒወት : ፈለግ : ተወጠነ፡፡ ኪዳነወልድግ : ዲያቆኑ : ለተጣፉበትና : ለተጠሩበት : ሒወት : አባትና : ልጅ፤ መምህርና : ደቀመዝሙር : ኾነው : ተያይዘው : ወደ : ድሬዳዋ : ወረዱ፡፡
የመዠመሪያው : ጥያቄ : ሲመለስ : ሌላ : ኹለተኛ : ጥያቄ : ከንጉሥ : ተፈሪ : መጣ… እንዲህ : ሲል፡-
ንጉሥ : ተፈሪ : የኢትዮጵያ : መንግሥት : ዐልጋ : ወራሽና : ባለሙሉ : ሥልጣን : እንደራሴ፡፡
ይድረስ : ከአለቃ : ኪዳነወልድ፡፡ እንደምን : ሰንብተኻል፤ እኒ : እግዚአብሔር : ይመስገን : ደኀና : ነኝ፡፡ ያገራችንን : የቋንቋ : ድኽነት : መቼም : የምታውቀው : ነው፡፡ ስለዚህ : ዲክሲዎኔር : እንዲገለበጥ : አዝዣለሁና : ለዚሁ : ሥራ : ላቶ : ብሩ : ረዳት : ኾነህ : የተቻለህን : ያኽል : ዐብራችሁ : እንድትሠሩ : ይኹን፡፡
የካቲት : ፳፯ : ቀን : ፲፱፻፳፩ : ዓመተ : ምሕረት
ዐዲስ : አበባ
አለቃ : ኪዳነወልድ : ክፍሌ : የንጉሥ : ጦማርም : ቢኾን : እንኳ፤ ከብዷቸው : እንደገና : ደግሞ : የተጠየቀው : አሠራርም : ዙሪያ : ጥምጥምነት : አላስፈላጊነቱ : ታይቷቸው : ግእዝን : ትቼ : ዐማርኛ : ልጽፍ : አይገባኝም : ብለው : ያንን : ዥምር : ብርሃናዊ : መጽሐፍ : በጽናትና : ቁርጠኝነት : ማዘጋጀቱን : ቀጠሉ፡፡
… በሥራ : ውለው : ማታ : ነፋስ : በመቀበል : ጊዜ : አንደ : ሐሳብ : ቢያገኙ : በማስታወሻ : ለመጻፍ : ከውጭ : ወደቤት : ይመለሳሉ፡፡ በምሳ : ወይም : በራት : ጊዜ : አንድ : ትርጓሜ : ቢታሰባቸው : ምግቡን : ትተው : ብድግ : ይላሉ፡፡ ሌሊትም : ተኝተው : ሳሉ : አንድ : ምስጢር : ቢገጥማቸው : ከመኝታቸው : ተነሥተው : መብራት : አብርተው : ይጽፋሉ፡፡
……………………………………………………………..……………………………..………
መዝገበ : ታላቱን : ሌት : ተቀን : እየደከሙ : እያለ : ከመታተሙ : በፊት : እንደ : መንገድ : ጠራጊ : የኾኑ : ኹለት : መጽሐፍት : ባ፲፱፻፳፮ ዓ.ም. አከታትለው : አሳትመዋል፡፡ አበገደ፣ ፊደልና : ፊደላዋሪያ፤ መዝገበ : ፊደላት፤ ሴማውያት : የሚባሉ፡፡ በመዝገበ : ፊደላት : ሴማውያት : የዠርባ : ሽፋን : ላይ : ስለመጩዥጪው : ሥራ : ሲያውጁ : እንዲህ : ብለዋል፡-
ይኸን : ጨቅላ : መጽሐፍ : የምታዩ : ኹሉ፤ ዐደራ : ስለእኔ : ማሪያም : ማሪያም : በሉ፤
በሆዴ : የለውን : የትምርት : ሽል አለጭንቅ : እንደወልድ : እንድገላገል፤ ከኻያ : ስድስቱ : ወንዶች : ፊደላት፤
አርግዣለሁና : መዝገበ : ቃላት፡፡
ስንት:እልፍ : አበው : ናቸው : አርግዘው : የሞቱ
ቀኝ : እጃቸው : ዐጥሮ : ጥፈት : በማጣቱ፤
እጂ : እንዳባቶቼ : እጅ : ተምሮ : ባይጥፍ፤
ከሆዴ : ባሎጣም : ይህ : ጨቅላ : መጽሐፍ፤
ለትምክሕት : አይደለም : ይህን : መናገሬ፤
ለማስቀናት : እንጂ : ሰነፈን : ገበሬ፤
ሐዋርያም : ሴጥፍ : ወዳርድእቱ : መንጋ፤
ቅኑ : አስቀኑ : ይላላ : ለምትበልጥ : ጸጋ፡፡
……………………………………………………………..……………………………..………
በመኻሉ : ፋሺስት : ኢጣልያ : ኢትዮጵያን : የወረረች : ጊዜ : የዚህ : ታላቅ : ሥራ : ወደፊት : እንዳይገፋ፤ ተደናቀፈ፡፡
ኪዳነወልድ : በባሕርያቸው : ቀጥተኛና : ግልጽ : ሰው : በመኾናቸው …
…ባ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. የንጉሠ : ነገሥቱን : ተመልሶ : መምጣትና : ከኢትዮጵያ : ዠምሮ : የመላ : አፍሪቃን : ነጻነት : ጥቂት : እንኳ : ሳያፍሩ : በመናገራቸው : ፋሺስቶች : በጨለማ : ውስጥ : ስላሰሯቸው : ያይናቸው : ብርሃን : ጠፋ፡፡
ታምራት : አማኑኤል : ይኸ : ሥራ : ከመታተሙ : በፊት : የሰጡትን : አስተያየት : ልንጠቅስ : እንወዳለን፡-
… የኢትዮጵያን : የጥንቱን : ትምህርት : ከሚያውቁት : ሊቃውንት : ዐማርኛንና : ግእዝን : ለማጣራት : ያለቃ : ኪዳነወልድን : ያኽል : የሚደክም : ብዙ : አልተገኘም … ሠላሳ : ዓመታት : ያኽል : የደከሙበት : ሥራ … ጠላት : አገራችንን : በወረረበት : ዘመን : እርሳቸው : ሲታሰሩ፣ ሲጋዙ : ያን : ያኽል : የደከሙበትን : ሥራ : የሚከውነው : አጥቶ : የብልና : የምስጥ : ምግብ : ኾኖ : መቆነጻጸሉ : ጉዳቱ : የራሳቸውና : የመላ : ኢትዮጵያ : ብቻ : ሳይኾን : ወሰን : ሳያግደው : ሰንደቅ : ዓላማ : ሳይለየው : ወገን : ለኾነው : ሰው : ኹሉ : ነው … ኪዳነወልድ : እንደ : ክፍለጊዮርጊስ : ኹሉ : ዕድለኛ : ኾነው : የጥበብ : ወራሽ : ደቀመዝሙር : አላጡም፡፡ ያንን : ንጉሣዊ : የማዘዣ : ደብዳቤ : ዐደራ : ያቀበሉት : ለሌላው : ልባም : ተማሪ - የጥሪው : ሦስተኛ : ሰው - ለዲያቆኑ : ደስታ : ተክለወልድ : ነበር፡፡ ደስታ : ተክለወልድ : ጐሽ : ውሃ : ወግዳ : ተወልደዋል፡፡ ሐምሌ : በባተ : ባ፲፰፻፺፫ ዓ.ም.፡፡
ምንጭ: ያሠርቱ : ምእት ፥ የብርእ : ምርት : ከ፲፻ : እስከ : ፳፻ : ድርሰት : ክፍል : ፩ ዻጉሜ : ፫ : ቀን : ፲፱፻፺፱ : ዓ.ም : በብርሃነመስቀል : ደጀኔ እና ጌታሁን : ሽብሩ፡፡ |
ይኼ:ሰው:ባ፲፰፻፹፪:ዓ.ም. እንደሳቸው:እንደ:ራሳቸው : ጥበብን : ከምንጩ : ለመጠጣት : ወደኢየሩሳሌም : የዘለቀው : የ፳ : ዓመቱ : የወንዛቸው : ልጅ : ኪዳነወልድ : ነበር፡፡ ዘመኑም : እሳቸው : ከሮሜ : በተመለሱ : በኹለተኛው : ዓመት : ኪዳነወልድ : ካገር : በወጣ : በዘጠነኛው : ዓመት : ባ፲፰፻፺፩ ዓ.ም. ተመልሰው : ወዳገራቸው : መጡ፣ መቼም : ተደርጎ : በማያውቅ : ኹኔታ : የሕዝቅኤልን : ረቂቅና : ጥልቅ : ያንድምታ : ትርጓሜ : ባ፲፰፻፲፮ ዓ.ም. ድሬዳዋ : ላይ : አሳትመው : አስረከቡ፡፡ በምላሹ : ይህ : ደብዳቤ : ተጽፎላቸው : ነበር። |
|
|
|
|
|
ኪዳነማርያም ጌታሁን |
|
|
|
|
|
አባ ኪዳነማርያም |
|
|
|
|
|
[1904 - 2002] |
|
ኪሩቤል በሻህ |
|
|
|
|
|
ካሳ ኃይሉ |
|
|
|
|
|
ካህሣይ ገ.እግዚአብሔር |
|
|
|
|
|
ካሳ ገብረህይወት |
|
|
|
|
|
ካሕሳይ አብርሃ ብስራት |
|
|
|
|
|
ክንፈሚካኤል ሲኖዳ |
|
|
|
|
|
ክነፈርግብ አታለል |
|
|
|
|
|
ክፍሉ ታደሰ |
|
|
|
|
|
ክፍሌ አቦቸር |
|
|
|
|